ራዕይ ና ተልዕኮ

ራዕይ
ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶች በዓይነት፣ በመጠንና በጥራት አድገው፣ በቀጣይ ዕድገት ላይ የተመሰረተና በዓለም ተወዳዳሪ የሆነ ዘመናዊ፣ ህጋዊና ፍትሃዊ የንግድና ግብይት ዘርፍ በ2017 ዓ.ም ተፈጥሮ ማየት፡፡
ተልዕኮ
በክልሉ የነጻ ገበያ መርህ የተከተለ ንግድና ግብይት በማዘመን፣ በማስፋፋት፣ ህጋዊነትና ፍትሃዊነት በማስፈን የሸማቹን ህብረተሰብና የንግዱን ማህበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡
የሴክተሩ ዕሴቶች
  • በዕቅድ እንመራለን፣
  • ፍትሃዊ አሳታፊና ዲሞክራሲያዊ አመራር መለያችን ነው፣
  • በማያቋርጥ ለውጥና መሻሻል እናምናለን!
  • ጊዜ እና የሰው ኃይል ካሉን ሀብቶች ሁሉ ቁልፍ ሀብቶቻችን ናቸው፣
  • ኪራይ ሰብሳቢነትን እንፀየፋለን፣
  • መረጃን ለልማት እናውላለን፣
  • ውጤት ያሸልማል፣
  • ተገልጋዮቻችን የሕልውናችን መሠረት ናቸው!
  • ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻችን ናቸው!
  • ለህዝባችን ብልፅግና እንተጋለን፡፡
ቅሬታ አቅራቢዎች መካሪዎቻች ናቸው፣