የክልሉ ን/ገ/ል/ቢሮ ኃላፊ መልዕክት

ሀገራችን የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን በንግድና በግብይት ዘርፍ ህጋዊና ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት፤ ምቹ የንግድ ስርዓት እና ጤናማ የገበያ ዉድድርን በመፍጠር የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ልማትን ለማረጋገጥ በ2013 በጀት ዓመት ዘጠኝ ወር በሴክተሩ የደረጃው የተጣሉ ግቦችን ከማሳካት ረገድ ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ፣ የመፈፀምና የማስፈፀም አቅም ከመገንባት፣ ወቅቱን የጠበቀ ድጋፋዊ ክትትል ከማድረግና ግብረ-መልስ ከመስጠት ረገድ በበጀት ዓመቱ በርካታ ሥራዎች ታቅደው ተከናውነዋል፡፡ ከዚህም የተነሳ በበጀት ዓመቱ የታቀዱ የልማትና መልካም አስተዳደር ግቦችና ተግባራት አበረታች አፈፃፀም  አስገኝቷል፡፡

የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታትና;የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ አጀንዳዎችን በላቀ ደረጃ ለመፈፀም ግብ ጥሎ በበጀት ዓመቱ ዕቅዱን ለማሳካት ከፍተኛ ርብርብ  እያደረገ ይገኛል፡፡

ንግዱን በማዘመን ሥራ በየነ-መረብ(ኦንላይን) አገልግሎት 101 መዋቅሮች ወረዳ ኔት የማስገባት ስራ የተከናውነ ሲሆኑ ቀሪዎችን በዚህ በጀት ዓመት ለማጠናቀቅ እየሰራን እንገኛለን፡፡

የገበያ መስረተ-ልማት ከማስፋፋት አንፃር በክልሉ በሚገኙ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች 100 ዘመናዊ የሰብል እና የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከላት በመንግስትና በግብርና ዕድገት ፕሮግራም እና በአርብቶ አደር ፕ ተገንብተዋል፡፡ ከነዚህ ዉስጥ  40 የሰብል፣40 የቁም እንሳሳት ግብይት ማዕከላት እና  20 የመንገድ ዳር ሼዶች ተገንብተው 86ቱ አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ ቀሪዎች 14ቱ የግብይት ማዕከላት በቢሮው ክትትልና ድጋፍ ተጠናቀው ወደ ስራ ይገባሉ፡፡

በንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን በንግዱ ዘርፍ ፍትሀዊና ትክክለኛ የአሰራር ስርዓት ከማስፈን አንፃር የተወሰኑ ጉድለቶች ቢኖሩም በርካታ ስራዎች ሰርተናል፡፡

ያለ ንግድ ፈቃድ የሚሰሩ፣ ፈቃድ ያላደሱ፣ በስነ-ልክና ሚዛን ሚያዛቡ፣ በነዳጅ ማደያዎች ካሊብሬሽን እና በመሳሰሉት ድንገተኛ ፍተሻና ምርመራ በማካሄድ  ህጋዊና አስተማሪ ዕርምጃዎች ተወስደው ወደ ስርዓቱ ገብተዋል፡፡

የሸማቾች ደህንነትንና የኮሮና ቫይረስን ጥንቃቄ አስመልክቶ ለንግዱም ሆነ ሸማቹ ማህበረሰብ የግንዛቤ ስራዎች በተለያዩ የሚዲያ አውታሮችና መድረኮች፣ በዘርፉ ጥናትን መሰረት ያደረገ የፓናል ውይይት መድረኮች አካሂደን ሸማቹ መብቱን በሚገባ የሚያስጠብቅበት ሁኔታ እየተፈጠረ ይገኛል፡፡

በሀገራችን በተከሰተው ወቅታዊ የፀጥታ ችግር እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ(ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ተከትሎ በክልላችን የሚገኙ የተወሰኑ ስግብግብብ  ነጋዴዎች በአንዳንድ የየግብርናና የፋብሪካ ምርቶች ላይ ምክንያታዊ  ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማድረግና  በህገ ወጥ የንግድ ሥራ ላይ ተሰማርተው በተገኙ  የንግዱ ማህበረሰብ ላይ  በርዕሰ መስተዳርሩ የሚመራ ከክልል ጅምሮ የተዋቀረው የዋጋ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል በህብረተሰቡ የጋራ ትብብር አስተዳደራዊ፣ህጋዊና አስተማሪ እርምጃዎች እየተወሰደ ይገኛል። እየተወሰዱ ካሉ እርምጃዎች በተጨማሪ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የንግድ ሥርዓቱ ወደ ተረጋጋ ሁኔታ እንዲመለስ ቢሮው ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራ ይገኛል።

በተለይ በከተማ የሚገኘው ሸማች ከታችኛው መዋቅርና ከገጠሩ አካባቢ በተሻለ በ8034 ነፃ የስልክ ጥሪና በአካልም በመገኘት ቅሬታ በቀረቡባቸው ቦታዎች ከፍትህ አካላትጋር በቅንጅት የሸማቹን መብት ለማስጠበቅ የተሄደበት አንዱ አግባብ ነው፡፡ ቢሮው ከኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ጋር በመተባበር ወቅታዊ የግብርና ምርት የገበያ ዋጋ መረጃ በነፃ የስልክ ጥሪ 6077 ለንግዱ ተዋንያን ተደራሽ እያደረገ ይገኛል፡፡

በግብርና ምርት ግብይት በህግ ማእቀፎች ወደ ኤክስፖርት ግብይት ቀይ ቦሎቄ፣ሲሊጥ፣እርግብ አተር፤ ዥንጉርጉር ቦሎቄ(ቡራ ቡርጂ)፤ ሰሊጥ እና ፒንቶ ምርቶች ወደ ኢሴክስ ማስገባት የተሰራ ያለው ሥራ ጥሩ ውጤት እያስገኘ ነው፡፡እንዲሁም በክልላችን ከማዕድናና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ከባለፈው ዓመት አንፃር ሲታይ ለውጥና ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል፡፡

የክልላችን የንግድና የገበያ ሥርዓቱን በማዘመን ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ሴክተራችን የሚሰጠው አገልግሎት የህብረተሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ ወደ ሴክተራችን የተቀላቀላችሁ አዳዲስ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት  የአገልግሎት አሰጣጥ ቅሬታ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት በየአከባቢው የሚስተዋልውን የኮንትሮባንድ እና ህገ-ወጥ ንግድ ችግሮችን ለመፍታትና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በጋራ የምንረባረብበት ወቅት መሆኑን የዘርፍ አመራርና ባለሙያ ከወትሮ በተለየ መንገድ ሥራውን በቁርጠኝነት መምራት ይጠበቅበታል፡፡!

አመሰግናለሁ!!

Error | የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ

Error message

  • Warning: Cannot modify header information - headers already sent by (output started at C:\xampp\htdocs\snnprstrad\includes\common.inc:2820) in drupal_send_headers() (line 1501 of C:\xampp\htdocs\snnprstrad\includes\bootstrap.inc).
  • Error: Class 'FeedsHTTPCache' not found in feeds_cron() (line 83 of C:\xampp\htdocs\snnprstrad\sites\all\modules\feeds\feeds.module).

Error

The website encountered an unexpected error. Please try again later.