የሴክተሩ ስልጣንና ተግባር
የንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል
- ንግድና ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ የተመቻቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ ያደርጋል፣
- በክልሉ ውስጥ ንግድን ለማስፋፋትና ለማጠናከር ቀልጣፋ የግብይት ስርዓትና ተገቢ የንግድ አሰራር እንዲሰፍን ያደርጋል፣
- አግባብ ባለው ህግ መሰረት የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ይሰጣል፣ ይቆጣጠራል፣ ይሰርዛል፣ የንግድ መዝገብ ያደራጃል፣
- በህግ በልዩ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ህገ-ወጥ የግብርና ምርቶች ዝውውር ይቆጣጠራል፣ ይከታተላል፣ በህግ አግባብ እርምጃ ይወስዳል፣
- በህግ በልዩ ሁኔታ ለሌላ አስፈፃሚ አካል የተሰጠው እንደተጠበቀ ሆኖ የግብይት ሥርዓትን በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፣
- ተገቢ ያልሆነ የንግድ አሰራርን ለመከላከል የሚያስችል የተሟላ ስርዓት ይዘረጋል፣ የንግድ ህጎች መከበራቸውን ያረጋግጣል፣ አፈጻጸማቸውን ይከታተላል፣
- በሕግ መሰረት ለሸማቾች ጥበቃ ያደርጋል፣ የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን ሥርጭት ይቆጣጠራል፣
- አግባብ ባለው አካል የዋጋ ቁጥጥር የተደረገባቸውን መሰረታዊ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች መተግበራቸውን ይቆጣጠራል፣
- አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያላቸው የንግድ እቃዎችና አገልግሎቶች የደረጃውን መስፈርት ማሟላታቸውን ይቆጣጠራል፣ ከተዘጋጀላቸው ደረጃ በታች ሆነው በተገኙት ላይ እርምጃ ይወስዳል፣
- የሀገሪቱን ህጋዊ ስነ-ልክ ስርዓት በአግባቡ መተግበሩን ይቆጣጠራል፣
- የንግድየዘርፍና የሙያ ማህበራት እንዲቋቋሙ ያበረታታል፣የተቋቋሙትንም እንዲጠናከሩ ያደርጋል፣
- ንግድን በማስፋፋት ረገድ የከተማና የገጠር፣ የከተሞች የእርስ በርስ ትስስር እንዲጠናከር ስትራቴጂ ይቀይሳል፣ ተግባራዊ ያደርጋል፣
- የኤግዚብሽንና ፕሮሞሽን ሥራዎችን በበላይነት ይመራል፣ ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣
- የግብርና ምርት ውጤቶች ጥራታቸው ተጠብቆ ተገቢውን ገበያ በአገር ውስጥና በውጭ እንዲያገኙ ያደርጋል፣
- ዓላማውን ለማስፈፀም የሚችሉ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናውናል፤